በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ

ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው።

ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ።

ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።