BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌደራል ኃይሎች ጋር የተካሄደው ግጭት "ሊፈጠር የማይገባ ነበር" አለ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከሰሞኑ በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የተካሄደው ግጭት "ሊፈጠር የማይገባ ነበር" አለ። "በግጭቱ ምክንያት" የተቋረጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ዳግም እንዲጀመር ለፌደራል መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡንም አስታውቋል።
ቀጥታ, የሳዑዲ መከላከያ ሚኒስትር ‘ትራምፕ እርምጃ ካልወሰዱ ኢራን መልሳ ትጠናከራለች’ አሉ
የአሜሪካው የዜና ድረ ገጽ አክሲዮስ የመከላከያ ሚኒስትሩ ልዑል ኻሊድ ቢን ሳልማን አርብ ዕለት ዋሽንግተን ውስጥ በተደረገ የግል ውይይት ላይ አሜሪካ ኢራንን ካልመታች አገዛዙ ተጠንክሮ ይወጣል ማለታቸውን በስፍራው የነበሩ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ህወሓት በትግራይ ክልል እና በፌዴራል መንግሥት መካከል ያለውን ጉዳይ ለመፍታት "ለንግግር ዝግጁ ነኝ" አለ
ህወሓት ትናንት ጥር 23/2018 ዓ.ም በይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባጋራውና ለአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ ላይ "ለሰላም እና መረጋጋት" ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቆ "እንደ ሁልጊዜው ለንግግር ዝግጁ ነኝ" ብሏል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለሕዳሴ ግድብ እስካሁን ምን አሉ?
ከቀናት በፊት በአባይ (ናይል) ጉዳይ ኢትዮጵያ እና ግብፅን ለማደራደር ጥያቄ ያቀረቡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ "ፍሰትን የሚያስቆም ግድብ" ሠርታለች አሉ። በዚህም ምክንያት ግብፅ ከናይል ወንዝ "በቂ ውሃ እንደማታገኝ" የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህንን ጉዳይ "መፍታት ይኖርብኛል" ሲሉ ተደምጠዋል። ለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ በተለያዩ ወቅቶች በጉዳዩ ዙሪያ ምን ተናገሩ?
ቪዲዮ, የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ማለት ይሆን?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቅራቢያ 'አቡሴራ' በተባለ አካባቢ የሚገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅዳሜ ጥር 2/2018 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣበት የአውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሲጠናቀቅ፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። 3,500 ሔክታር መሬት የሚሸፍነው ይህ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል።
ቪዲዮ, ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ያላት አሜሪካ ለምንድን ነው በሌሎች አገራት ነዳጅ ላይ ዐይኗን የጣለችው?
አሜሪካ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ቢኖረትም በሌሎች አገራት ውስጥ ባሉ የነዳጅ ክምችቶች ላይ ዘወትር ትረኩት ደታርጋለች። ለዚህ በበርካታ አገሮች ጦርነት ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ስትሳተፍ ቆይታለች። በቅርቡም በቬንዙዌላ ሰጥ ቀጥተኛ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ መሪዋን ይዛ ወስዳለች። ከዚያም በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቬንዙዌላ የነዳጅ ሀብት ላይ አሜሪካ ያላትን ፍላጎት በይፋ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ቪዲዮ, “ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን” ፕሬዝዳንት ኢሳያስ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገራቸው ቴሌቪዥን ��ር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ላለው ውጥረት እና ለተፈጠረው ችግር ከጀርባ ሆኖ የሚገፋ ወገን እንዳለ ተናግረዋል። ጦርነት ሊከሰት የሚችልበት እድል እንዳለ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ ለዚህም ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ “ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን” ብለዋል።
ቪዲዮ, አሜሪካ ዐይኗን የጣለችው በማዱሮ ላይ ወይስ በቬንዙዌላ ነዳጅ ላይ?
አሜሪካ ማዱሮ ላይ በዕጽ እና በጦር መሳሪያ ዝውውር ብትከሳቸውም ዋነኛ ትኩረቷ ቬንዙዌላ ባላት የተትረፈተፈ የነዳጅ ሀብት ላይ እንደሆነ ይነገራል። ትራምፕም ይህንን ሳይደብቁ ተገቢው ሽግግር እስኪደረግ ድረስ ቬንዙዌላ በአሜሪካ እንደምትመራ እና ኩባንያዎቿ የነዳጅ ምርት ሥራውን እንደሚረከቡ በግልጽ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, የሶማሊላንድ ቀጣዩ ዕውቅና የማግኘት ፈተና፡ ቀጥሎ ማን ዕውቅና ይሰጣታል?
እስራኤል ለሶማሊላንድ አገርነት ይፋ ዕውቅና መስጠቷን ተከትሎ የሶማሊላንድ እና የሶማሊያ እንዲሁም የቀጣናው ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ጥያቄ መነሳት ጀምሯል።
ቪዲዮ, ይህ የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪው ሙላቱ አስታጥቄ የመጨረሻ የሙዚቃ ሥራው ይሆን?
የሙላቱ የሙዚቃ ጉዞ አስርት ዓመታትን ያስቆጠረ ነው። የተወለደው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዋ ከተማ ጅማ ነው። ነገር ግን ለዩናይትድ ኪንግደም ትልቅ ቦታ አለው። ትምህርቱን በዌልስ ነው የተከታተለው። ሙላቱ ወደ ሙዚቃው ዓለም እንዴት ገባ? ከዚህ በኋላስ መድረክ ላይ እናየው ይሆን?
ቪዲዮ, የሁለት መሪዎች ፉክክር እንዴት ፖለቲካዊ ቀውስ ፈጠረ?
ነጻነቷን ከተቀዳጀች ጥቂት ዓመታትን ያስቆጠረችው ደቡብ ሱዳን እስካሁን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አልቻለችም። ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የቀድሞ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ፤ መልሰው ወደ አለመግባባት ገቡ፤ በድጋሚ ወደ ክብ ጠረጴዛ አመሩ። በድጋሚ ውጥረቱ እየጨመረ ይገኛል። የሁለቱ መሪዎች ውሳኔ አገሪቱ ወደ መረጋጋት ሊያሸጋግር ካልሆነም አዲስ ቀውስ እንዲፈጠር ምክንያት ሊሆን ይችላል። ለመሆኑ በደቡብ ሱዳን ምን እየተካሄደ ነው?
ቪዲዮ, የካንሰር ላለባቸው ህጻናት ህክምና በሚል የተሰበሰበው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዴት ሊጭበረበር ቻለ?
ቢቢሲ ካንሰር ላለባቸው ልጆች ህክምና በሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እየተሰበሰበ መሆኑን ደርሶበታል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው ለህጻናቱ ህክምና እንደማይውል ታውቋል። ለመሆኑ ይህንን ገንዘብ የሚያሰባስቡት እነ ማን ናቸው? የዚህ ገንዘብ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?
አነጋጋሪ ጉዳይ
ኢትዮጵያ በግልባጭ እንድታውቀው የተደረገው የትራምፕ የሕዳሴ ግድብ ድርድር ጥሪ ደብዳቤ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለግብፁ ፕሬዝዳንት በጻፉት ደብዳቤ ኢትዮጵያ በገነባችው በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምክንያት የተፈጠረውን አለመግባባት በዘላቂነት ለመፍታት እንደተነሱ ገልጸዋል። ነገር ግን ደብዳቤው በቀጥታ ለግብፅ፣ የግድቡ ባለቤት ለሆነችው እና ዋነኛዋ ተደራዳሪ ለሆነችው ኢትዮጵያ ግን በግልባጭ ነው እንድታውቀው የተደረገው። ይህ ምን ማለት ነው? የትራምፕ ፍላጎት ምን ሊሆን ይችላል? የደብዳቤው ይዘት እና ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ምላሽ ልትሰጥ ትችላለች?
ትራምፕ ግብፅ "በቂ ውሃ እንዳታገኝ" ያደረገውን የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ "መፍታት አለብኝ" አሉ
ከቀናት በፊት በአባይ (ናይል) ጉዳይ ኢትዮጵያ እና ግብፅን ለማደራደር ጥያቄ ያቀረቡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ "ፍሰትን የሚያስቆም ግድብ" ሠርታለች አሉ። በዚህም ምክንያት ግብፅ ከናይል ወንዝ "በቂ ውሃ እንደማታገኝ" የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህንን ጉዳይ "መፍታት ይኖርብኛል" ሲሉ ተደምጠዋል።
እየተቀየረ ያለው በህወሓት ቁጥጥር ሥር የነበረው የትግራይ ፖለቲካ ምኅዳር
ከዓመታት ግጭት እና የህወሓት የበላይነት በኋላ በትግራይ አዳዲስ ፓርቲዎች እና የፖለቲካ ተዋናዮች ብቅ እያሉ የፖለቲካ ምኅዳሩ እየተቀየረ ነው። በአሁኑ ወቅት በክልሉ የፖለቲካዊ ፓርቲዎች መበራከት ምን ተስፋ እና ተግዳሮትን ይዞ ይመጣል? ወደ 15 እንደደረሱ የሚነገረው ፓርቲዎች ለሕዝቡ ምን ዓይነት ርዕየተ ዓለም እና ሃሳብ ይዘውለት መጡ?
በዋግ ኽምራ ዞን ካምፕ ውስጥ በነበሩ ሚሊሻዎች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ቢያንስ 36 ሰዎች ተገደሉ
በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስብሰባ ላይ በነበሩ የሚሊሻ አባላት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ቢያንስ 36 ሰዎች መገደላቸውን አንድ የሰሃላ ሰየምት ወረዳ አመራር፣ የጤና ባለሙያ እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። በአካባቢው የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች ጥቃቱ የተፈጸመው "በስህተት" እንደሆነ መናገራቸውን የወረዳ አመራሩ እና ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ፑንትላንድ የአይኤስ ተዋጊ የሆኑ 23 "ኢትዮጵያውያንን" መያዟን አስታወቀች
የሶማሊያ ግዛት የሆነችው ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ በቁጥጥር ሥር ካዋለቻቸው 53 የእስላማዊው ታጣቂ 'ኢስላሚክ ስቴት' (አይኤስ) ተዋጊዎች መካከል ግማሽ ገደማው "ኢትዮጵያውያን" መሆናቸውን አስታወቀች። የፑንትላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር ማሕሙድ አይዲድ ዲሪር "ከየትም ይምጡ ከየት፣ ከሩቅም ይሁን ከቅርብ ሁሉም አንድ ዓይነት ርዕዮተ ዓለም የሚከተሉ ናቸው" ብለዋል።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
ከቢሾፍቱው የአውሮፕላን ማረፊያ የዲዛይን አማካሪዎች አንዱን የመሠረተችው ዕውቅ አርክቴክት ዛሃ ሐዲድ ማን ናት?
ዛሃ ሐዲድ ከኪነ ሕንጻ ጋር በተያያዘ በዓለም ስመ ጥር ከሆኑ ባለሙያዎች አንዷ ነበረች። ከቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ የዲዛይን አማካሪዎች አንደኛው ዛሃ ሐዲድ ያቋቋመችው 'ዛሃ ሐዲድ አርክቴክትስ' ነው። ሌላኛው ተቋም ደግሞ ዳር ይሰኛል።
ለጉንፋን ያለሐኪም ትዕዛዝ መድኃኒቶችን መውሰድ ለከፋ አደጋ እንደሚያጋልጥ አስበው ያውቃሉ?
በቀላሉ የሚድኑ ሕመሞች ያጋጠመን በመሰለን ጊዜ መጀመሪያ የምናደርገው ከዚህ ቀደም ያሻሉንን መድኃኒቶች በድጋሚ ገዝቶ መውሰድ ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን በዙሪያችን ላሉ ሰዎችም ያለ ሐኪም ትዕዛዝ 'ፍቱን ናቸው' ብለን ያሰብናቸውን መስጠትን ያካትታል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
"እናቴ መርዝ ልታበላኝ ስትል ደረስኩባት…" ሁላችንም ትንሽ ትንሽ 'እያበድን' ይሆን?
ስኪዞፍሪኒያ የሚባል የአእምሮ ጤና መታወክ እንዴት ያለ ነው? ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ፒኤችዲ ሠርተውበታል። ለ20 ዓመት ተመራምረውበታል። በስኪዞፍሬኒያ የሚሰቃዩ በርካታ ታካሚዎች ነበሯቸው፤ አሏቸው። ፕሮፌሰሩ ነገርን በአጭር የማስረዳት ፀጋ አላቸው። ይህን የአእምሮ በሽታ እንዲህ ይገልጹታል። "ነገሩ የማርያምን ብቅል ሲፈጩ መዋል ነው" ይሉታል። ምን ማለታቸው ነው?
ማዱሮ ከሥልጣን ይወርዳሉ ብሎ የተወራረደ አንድ ግለሰብ 436 ሺህ ዶላር አሸነፈ
ማዱሮ ከመታሰራቸው በፊት የቬንዙዌላው ፕሬዝደንት ከሥልጣን ይወርዳሉ ብሎ ቁማር የተጫወተ አንድ ግለሰብ 436 ሺህ ዶላር ማሸነፉ ተሰማ። አንዳንዶች ግለሰቡ ምናልባትም የውስጥ መረጃ ይኖረው ይሆናል ሲሉ ጥርጣሬያቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
የእስራኤል እና የኢራን ግጭት
አደገኛው ታጣቂ ቡድን አይ ኤስ በምዕራቡ ዓለም ዳግም እየተጠናከረ ይሆን?
አይኤስ በመካከለኛው ምሥራቅ የነበረውን ድጋፍ እያጣ ከመጣ ወዲህ በአፍሪካ የተለያዩ አገራት ውስጥ እግሩን እያስገባ ነው። በምዕራብ አፍሪካ አገራት 12ሺህ የሚደርሱ ተዋጊዎች ያሉት አይኤስ በጎረቤት አገር ሶማሊያ ውስጥም ይንቀሳቀሳል። በዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ በሞዛምቢክ እና ናይጄሪያም ቡድኑ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል።
በቀይ ባሕር የጦር ሰፈር ለማቋቋም የተቃረበችው ሩሲያ ለቀጣናው ምን ይዛ ትመጣለች?
ከከተፎካካሪዎቿ ዘግይታ ወደ ቀይ ባሕር ወታደራዊ ኃይሏን ለማስፈር የተቃረበችው ሩሲያ በወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ላይ ላይ አዲስ ኃይል ትሆናለች። በአፍሪካ የመጀመሪያዋን የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ለመመሥረት ስትጥር የቆየችው ሩሲያ አሁን ፍላጎቷን ዕውን ለማድረግ ተቃርባለች። ይህ የሩሲያ ኃይል ወደ ቀጣናው መምጣት ምን ይዞ ይመጣል?
አሜሪካ የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያቀረበችበት የዋይት ሐውስ እንግዳ፡ አህመድ አል ሻራ
አዲሱ የሶሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በአግባቡ የተተኮሰ ሱፍ ለብሰው፣ ፀጉራቸውን ወደ ኋላ አበጥረው ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ሲመጡ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንዳሉ ያስታውቃል። አሁን የትግል ልብሳቸውን ትተው፣ አዲስ ስም ይዘው በዓለም ላይ ካሉት በጣም ኃያላን መሪዎች ጋር ይጨባበጣሉ።
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል የሆነችው የአይሁዶች አገር እስራኤል እንዴት ተመሠረተች?
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል እና ብቸኛዋ የአይሁዶች አገር የሆነችው እስራኤል በዙሪያዋ ካሉ አገራት ሁሉ በዕድሜ ትንሿ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ በአውሮፓውያኑ 1948 የእስራኤል እንደ አገር መመሥረት በአካባቢው አሁን ድረስ እየተካሄደ ያለ ለውጥን አስከትሏል። ለመሆኑ በየዕለቱ የዓለም መገናኛ ብዙኃን ስሟን ሳያነሱ የማያልፏት ይህች አገር እንዴት ተመሠረተች?
እስራኤል 15 የጦር አውሮፕላኖችን አሰማርታ ኳታር ውስጥ የፈጸመችው ጥቃት
በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ እስራኤል ጥቃት የፈጸመችው በርካታ የሐማስ ፖለቲካ ቢሮ ባለሥልጣናት በሚኖሩበት የመኖሪያ አካባቢ ላይ ነው። በዚህ ጥቃት አስከ ስምንት የሚደርሱ ፍንዳታዎችን እና ከፍተኛ ጭስ በዶሃ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ማየታቸውን ዓይን እማኞች ተናግረዋል። ከጥቃቱ ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እስራኤል ለተፈጸመው ጥቃት በይፋ ኃላፊነቱን ወስዳለች።
የእስራኤል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ተጠይቆ የነበረው ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን
የጠቅላይ ሚኒስትር ዴ��ድ ቤን ጉርዮን መንግሥት በዓለም ታዋቂ የሆነው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ለእስራኤል ፕሬዝዳንትነት እንዲሆን ካጩት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤል አምባሳደር አባ ኢባን አንስታይንን እንዲያነጋግሩ ተደረገ።
የተመለሱ ጥያቄዎች
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሾፍቱ እንዲሆን ለምን ተመረጠ?
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፍ የሚባለው የአውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ያህል በሚርቅ ቦታ ላይ ለመገንባት ሥራ ጀምራለች። ይህ አውሮፕላን ማረፊያ መሃል አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኘው በብዙ እጥፍ የሚበልጡ መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል። ይህንን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ለምን አሁን መገንባት አስፈለገ? ቦታውስ ለምን ተመረጠ?
በሴቶች ላይ እየበረታ ከመጣው የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቃት እንዴት ራስን መጠበቅ ይቻላል?
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እስከ 58 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች በኦንላይን ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ዒላማ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ድርጅት አስታውቋል።
ሌላ ዕይታ
ቢቢሲ አማርኛን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ
ከማኅደራችን
ማርበርግ ቫይረስ: የመጀመሪያው ታማሚ እና ሦስት መሪዎቿን ያጣችው የጂንካ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን
ከሌሊት ወፎች የሚነሳው የማርበርግ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ አንድ ወር ሊደፍን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። የጤና ሚኒስቴር፤ እንዴት በሽታው በጂንካ ከተማ ሊነሳ እንደቻለ እስካሁን አልገለጸም። ለመሆኑ በጂንካ የመጀመሪያው ታማሚ ማን ነበር? የበሽታው መነሻ የሆኑት የሌሊት ወፎችን እና የመጀመሪያውን ታማሚስ ምን አገናኛቸው? ቢቢሲ ባደረጋቸው በርካታ ቃለ መጠይቆች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ መረጃዎች አሰባስቧል።
"ቢገድሉኝ ይሻል ነበር"፡ የሴቶችን ሕይወት እያበላሸ ያለው የተዘነጋው የአማራ ክልል ጦርነት
ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ግጭቱ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ሰቆቃ ትኩረትን አላገኘም። ቢቢሲ ለወራት ባካሄደው ክትትል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የመደፈር እና የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መረጃ አግኝቷል።
በብርሌ ፍቅር የወደቁት ፈረንጅ 'ብርሌ ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ አለ' ይላሉ
ሰሞኑን አረቄ ብሔራዊ አጀንዳ ሆና የማኅበራዊ ሚዲያ አናት ላይ ወጥታ ነበር። ጠጅ ቢሆን አናት ላይ አይወጣም፤ ወደ ጉልበት ነው የሚወርደው። ጠጅ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳይ ሆኖ የሥነ መንግሥቱ አናት ላይ ወጥቶ፣ 'ብሔራዊ አጀንዳ' የነበረው በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ዘመን ነው። ድሮ ጠጅ በብርሌ ይቀርብ ነበር። ከዚያ በብርሌ ይጠጣ ጀመር። ጠጅ ግን እንደ አረቄ ማንም ‘ተራ ዜጋ’ ብድግ አድርጎ አያንደቀድቀውም።ብርሌ ውስጥ የመደብ ታሪክ አለ። የዘመን ታሪክ አለ። የጭሰኛና የመሳፍንት ታሪክ አለ። ያልተሳከረ።
ዓለምን የሚዞረው ኢትዮጵያዊ ከዩቲዩብ ምን ያህል ያገኛል?
ከተከፈተ በዚህ ወር 20 ዓመት የሆነው የቪዲዮ ማጋሪያው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ዩቲዩብ ለብዙዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ፈጥሯል። ከእነዚህም መካከል አቤል ብርሃኑ አንዱ ነው፤ በዩቲዩብ አማካኝነት 62 ሀገራትን ዟሯል። ያልረገጠው አህጉር አንታርቲካን ብቻ ነው። ሁሉንም የአሜሪካ ግዛቶች አካሏል። ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ዩቲዩብ ላይ የቆየው አቤል ከዩቲዩብ ምንያህል ያገኛል?
ቪዲዮ, በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለ���ቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?
"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀ��ም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።













































































































