ከወዳጆችዎ ጋር ሊያቀያይምዎ የሚችለውን የሞባይል ስልክ አጠቃቀምዎን እንዴት ማስተካከል ይችላሉ?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ስልኮቻችን ለግንኙነቶቻችን ጥሩ እንዳልሆኑ ሁላችንም እናውቃለን፣ ነገር ግን ይህ በቀን ብዙ ወደ ስልካችን ከማማተር አያግደንም።
ይህ ስልካችን ላይ በማቀርቀር አንድን ሰው ችላ ማለት በጊዜ ሂደት ወደ ዕለት ተዕለት ልማድ ይቀየራል።
ይህ ወዳጆችን ችላ እንዲሉ በማድረግ ግንኙነትዎን ሊጎዳ ይችላል፣ እና የወላጆች ስልክ አዘውትሮ መጠቀም ሕጻናት ልጆች ከአቻዎቻቸው ጋር ያለውን ግንኙነት ይጎዳል፤ በዕድሜ ከፍ ያሉት ልጆች ደግሞ ለራሳቸው ያላቸውን ግምት በእጅጉ ሊጎዳ ይችላል።
ከስልክዎ ጋር በተያያዘ ራስዎን መቆጣጠር ባለመቻልዎ፣ ራስዎን ከመተቸት ይልቅ፣ ስልኮቻችንን በምናነሳበት ወቅት ለምን እና መቼ እንደምናነሳ ንቁ ሆኖ ማተኮር የበለጠ ውጤታማ ሊሆን ይችላል ሲሉ አንድ የሥነ ልቦና ባለሙያ ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለንደን ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ኬትሊን ሬጌህር ከሌላ ሰው ጋር ሲሆኑ ከቀልብዎ ሳይሆኑ ስልክዎትን ከማንሳት ለመቆጠብ አንድ ቀላል መንገድ ይመክራሉ።
እጅዎትን ወደ ስልክዎ ሲልኩ፣ ስልክዎትን ለምን እያነሱ መሆኑን ለሌላኛው ሰው ይንገሩ፣ እና ከስልክዎት ጋር ያለዎትን ጉዳይ ሲጨርሱ አስቀምጠው ወደ ጉዳዮ ይመለሱ።
በጣም ቀላል ሊመስል ይችላል፣ ነገር ግን ዶ/ር ሬጌር ይህ ትንሽ ለውጥ ባህሪያችንን ለማረቅ ይረዳል ይላሉ።
ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሳናስብበት መልዕክቶችን ለማየት፣ ማሳወቂያዎችን ስናይ ወይም "አንድ ነገር በፍጥነት ለማየት" ስልካችንን እናነሳለን።
አስፈላጊው ነገር ግልጽ መሆን ነው፣ ስለዚህ ማየት ያለብዎት መልዕክት ከደረሰዎ አብሮዎት ላለው ሰው "ለዚህ መልስ መስጠት ብቻ ነው የሚያስፈልገኝ፣ ከዚያ እንደገና ትኩረቴን ያገኛሉ" ብለው ይናገሩ።
"የምሳፈርበትን ባቡር መነሻ ሰዓት ማየት አለብኝ" ወይም "ለእናቴ ምላሽ እየሰጠሁ ነው" ብለው በመናገር፤ ስልክዎን በመደነፍስ የመነካካት ልምድዎን ይተዋሉ፤ ከጎንዎ ላለው ሰውም አሁንም አስፈላጊ መሆኑን ያሳያሉ።
"ሌላኛው ሰው ችላ ተብያለሁ ብሎ እንዳያስብ ያደርገዋል" ይላሉ ዶ/ር ሬጌር።
"እንዲሁም ኃላፊነት የሚሰማው ሰው ያደርጋችኋል፣ ምክንያቱም ወደ ሌሎች መተግበሪያዎች የመዘዋወር ዕድልዎ ዝቅተኛ ነው።"
ይህን ማድረግ ግንኙነቶችዎንም ለማሻሻል ይረዳል።
በሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልቦና ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ክሌር ሃርት ስለ ግንኙነታቸው እና ስለ ስልክ አጠቃቀማቸው ከ196 ሰዎች ጋር በመነጋገር የተደረገ ጥናትን መርተዋል። በአጠቃላይ ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት እርስዎ በወዳጅዎ ስልክ ላይ ማተኮር ምክንያት ችላ እንደተባሉ በተሰማዎት ቁጥር ግንኙነታችሁ እየተጎዳ ይሄዳል።
"ሁሉም ሰው በተመሳሳይ መንገድ ምላሽ አይሰጥም" ይላሉ ዶ/ር ሃርት። "በባህሪው ላይ የተመሰረተ ነው፤ ነገር ግን አንድ ሰው ችላ እንደተባለ ከተሰማው፣ የበቀል እርምጃ ሊወስድ ይችላል።
"የራሳቸውን ስልክ ያነሳሉ፣ እና እያንዳንዱ አጋር እንደተገለለ ወይም በስክሪኑ ላይ ካለው ነገር ያነሰ ዋጋ እንደሌላቸው ስለሚሰማው አደገኛ አዙሪት ይሆናል።"















