በወርቅ የተሠራው መጸዳጃ በ12 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

አሜሪካ የተሰኘው መጸዳጃ በጣሊያናዊው አርቲስት ማውሪዚዮ ካቴላን የተሠራ ነው

የፎቶው ባለመብት, Sotheby's

በወርቅ የተሠራው መጸዳጃ በ12 ሚሊዮን ዶላር መሸጡ ታወቀ። መጸዳጃውን የገዛው በአሜሪካዊው ሮበርት ሪፕሊ የተመሠረተው 'ብሊቭ ኢት ኦር ኖት' ተቋም ነው።

'አሜሪካ' የተሰኘው መጸዳጃ በጣሊያናዊው አርቲስት ማውሪዚዮ ካቴላን የተሠራ ነው። አገልግሎት የሚሰጠው መጸዳጃ በ101.2 ኪሎ ግራም፣ ባለ 18 ካራት ወርቅ የተሠራ ነው።

የመጀመሪያው ተመሳሳይ መጸዳጃ ኒውዮርክ በሚገኘው ጉገንሃይም ሙዚየም በ2016 በሕዝብ መጸዳጃ ቤት ተገጥሞ የቆየ ቢሆንም ከሦስት ዓመታት በኋላ ከኦክስፎርድሻየር ቤተ መንግሥት መሰረቁ ተገልጿል።

ሁለተኛ የወርቅ መጸዳጃ መኖሩ ይፋ ከሆነ በኋላ ማክሰኞ ዕለት በኒውዮርክ ከተማ ሶቴቢ በተሰኘው የአጫራች ድርጅት ለገበያ ቀረቧል። 101 ኪሎ ግራም የሚመዝን መጸዳጃ ቤት አንድ ተጫራች ብቻ ማግኘቱ ታውቋል።

የመነሻ ዋጋው የሚወሰነው በወርቅ ትክክለኛ የገበያ ዋጋ ማለትም በ10 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ አጫራቹ ተናግሯል።

በታዋቂው የአሜሪካ ተቋም 'ሪፕሊስ ብሊቭ ኢት ኦር ኖት' እንደተገዛም ገልጿል። ተቋሙ በኢንስታግራም ገጹ ላይ "በደስታ እንጠቀመዋለን" ሲል በመጻፍ ገዢው መሆኑን ገልጿል።

የመዝናኛ ተቋሙ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ እንግዳ ነገሮችን ጨምሮ የውሃ መዝናኛ መስህቦችን በማቅረብ ይታወቃል።

ታዋቂዋ ኪም ካርዳሺያን የማሪሊን ሞንሮ ንብረት የሆነውን ቀሚስ እንድትለብስ በመፍቀድ በ2022 የመገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

እንግዶች "የወርቅ መጸዳጃውን እንዲጠቀሙ" ለመፍቀድ የሚያስችሉ "አማራጮችን እየመረመሩ" እንደሆነ ተገልጿል።

"እንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ ትልቅ ዕቅድ እና ሁሉም ነገር በትክክለኛው አቅጣጫ እንዲሄድ ለማረጋገጥ ድፍረት ይጠይቃል" ሲል ሪፕሊ አክሏል።

የሥነ ጥበብ ሥራው ለካቴላን ሁለተኛውን ከፍተኛ ዋጋ ያስመዘገበ ጨረታ ሆኖ ተጠናቋል። ሂትለር ተንበርክኮ የሚታይበት ሥነ ቅርጹ በ2016፣ በ17.2 ሚሊዮን ዶላር ተሸጧል።

ሶቴቢ ገዢው ታዋቂ የአሜሪካ ብራንድ እንደሆነ ተናግሯል

የፎቶው ባለመብት, Sotheby's

የመጀመሪያውን መጸዳጃ ቤት በጉገንሃይም በነበረበት ወቅት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች እንደተጠቀሙበት ይገመታል።

እአአ መስከረም 14 ቀን 2019 አምስት ሰዎች በብሌንሃይም ቤተ መንግሥት ገብተው 4.8 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣውን የወርቅ መጸዳጃ ሰርቀው በቮልስዋገን መኪና አመለጡ።

ዝርፊያው እና ከዚያ በኋላ የነበረው የፍርድ ሒደት በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

በ2024 የ40 ዓመቱ ጄምስ ሺን በስርቆት እና በወንጀል የተገኘ ንብረትን በማዘዋወር ጥፋተኛ መሆኑን አምኗል። የ39 ዓመቱ ማይክል ጆንስ በበኩሉ በመጋቢት ወር በስርቆት ጥፋተኛ ተብሏል። ሁለቱም በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ላይ ታስረዋል።

የ36 ዓመቱ ፍሬድ ዶ የወንጀል ንብረትን ለማዘዋወር በማሴር ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የእስር ቅጣት ተፈርዶበታል።