ቢቢሲ በጋዛ የሁለት ዓመት ጦርነት የእስራኤል ጦር ያደረሰውን ውድመት ተመለከተ

በጋዛ ከተማ ምሥራቃዊ ክፍል ሼጃኢያ አካባቢ
የምስሉ መግለጫ, በጋዛ ከተማ ምሥራቃዊ ክፍል ሼጃኢያ አካባቢ

የጋዛ ከተማን ከፍ ካለ ስፍራ ሆነው ሲመለከቷት ጦርነቱ ያስከተለውን ውድመት የሚሸሽግ አንዳችም ነገር የለም።

ጋዛ መሆኗን የሚገልፁ ምልክቶች እና ማስታወሻዎች እንዳለ ወድመው የተተኩት በፍረስረራሾች ክምር ነው።

ከጋዛ ከተማ አንደኛው ወገን ከቤት ሃኖን ወደ ሌላኛው አቅጣጫ 180 ዲግሪ ዞረው ቢመለከቱ የሚመለከቱት የሕንጻ ፍርስራሾችን ነው።

በጋዛ ከተማ ከርቀት ድሮ ሕንጻ እነደነበር የሚያስታውቅ የሕንጻ ፍርስራሽ ይታያል።

በዚህች ከተማ የነበረው ውበት አሁንም የሚገኝ ወይም ከዚህ ቀደም በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ማስጠጋቱን ምስክር የሚሆን አንድም ነገር አይገኝም።

ይህ አካባቢ የእስራኤል መከላከያ ኃይል ከሐማስ ጋር ጦርነት እንደጀመረ ከገባባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ነው።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሐማስ ጠንካራ ቁጥጥር ባለው የዙሪያው አካባቢዎች ራሱን መልሶ እያደራጀ ጥቃት ሲከፍት የእስራኤል ጦርም በተደጋጋሚ ጥቃት ፈጽሞበታል።

እስራኤል በጋዛ የመገናኛ ብዙኃን በነጻነት እንዲዘግቡ አትፈቅድም።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

አሁንም የጋዜጠኞች ቡድንን፣ ቢቢሲን ጨምሮ፣ በእስራኤል ቁጥጥር ሥር በሚገኘው የሰርጡ አካባቢ የወሰደው ጦሩ ነው።

ይህ አጭር ጉብኝት እጅግ በጣም ቁጥጥር የሚደረግበት እንዲሁም ፍልስጤማውያንን ማናገር ያልተፈቀደበት ወይም ወደ ሌሎች ጋዛ አካባቢዎች መሄድ ያልተፈቀደበት ነበር።

በእስራኤል ውስጥ ወታደራዊ የቅድመ ምርመራ ሕጎች ያሉ ሲሆን ይህም ጦሩ በመገናኛ ብዙኃን የሚወጡ ጽሑፎችን ከመታተማቸው በፊት እንዲያይ ያስገድዳል። ቢቢሲ በዚህ ዘገባ ላይ ሙሉ በሙሉ የኢዲቶሪያል ቁጥጥር አድርጓል።

ቢቢሲ ጉብኝት ባደረገባቸው አካባቢዎች ስለደረሰው ውድመት መጠን የተጠየቁት የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ናዳቭ ሾሻኒ ያ "ግባችን አይደም" ሲሉ መልሰዋል።

"ግባችን አሸባሪዎቸን መዋጋት ነው። እያንዳንዱ ቤት ለማለት በሚያስችል መልኩ የምድር ለምድር ዋሻ መሹለኪያ ወይም የተጠመዱ ፈንጂዎች ወይንም ሮኬት ማስወንጨፊያ ወይንም የዓልሞ መተኮሻ ማማ አለው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

"በፍጥነት እየነዱ በደቂቃ ውስጥ የእስራኤላዊ አያት ወይንም ልጅ መኖሪያ ሳሎን ውስጥ መገኘት ይችላሉ። ያ ነው የሆነው መስከረም 26"።

መስከረም 26 2016 ዓ.ም. ሐማስ ድንገተኛ ትቃት ሰንዝሮ ከ1,100 በላይ ሰዎችን ሲገድል 251 ሰዎችን ደግሞ አግቶ ወስዷል።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእስራኤል ጦር በጋዛ የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጦርነት ተከትሎ ከ68,000 በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሌተናል ኮሎኔል ሾሽኒ በዚህ ሳምነት አስከሬን የተመለሰውን ታጋች ኢታይ ክሄን ጨምሮ የበርካታ ታጋቾች አስከሬን በአከባቢው መገኘቱን ተናግረዋል።

ሐማስ አሁንም የተጨማሪ የታጋቾችን አስከሬን ለማስረከብ በፍርስራሾቹ ውስጥ ፍለጋ እያካሄደ ነው።

ቢቢሲ እና ሌሎች ጋዜጠኞች የተጓዙበት የእስራኤል መከላከያ ጦር ሠፈር የሚገኘው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራም የሰላም ዕቅድ መሰረት ከተሰመረው ቢጫ መስመር ጥቂት መቶ ሜትሮች ርቀት ላይ ነው።

የእስራኤል ጦር ቢጫውን መስመር ለሐማስ ተዋጊዎች እና ለነዋሪዎች ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ቀስ እያለ በጉልህ የሚታዩ ምልክቶችን እያስቀመጠ ነው።

የሐማስ ተዋጊዎች በጋዛ ከተማ አካባቢ

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, የሐማስ ተዋጊዎች በጋዛ ከተማ አካባቢ

የተኩስ አቁም ስምምነቱ አንድ ወር ሊሞላው ቢሆንም የእስራኤል ኃይሎች ግን አሁንም "በየቀኑ ማለት በሚያስደፍር መልኩ" በቢጫ መስመር አካባቢ ከሐማስ ታጣቂዎች ጋር እየተዋጉ መሆኑን ይናገራሉ።

የነሐስ ቀለም ያላቸው የጥይቶች ክምር የተካሄዱትን ተኩሶች ያመለክታሉ።

ሐማስ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን "መቶ ጊዜ" ጥሳለች ሲል የሚከስ ሲሆን የጤና ሚኒስቴሩ ደግሞ በዚህ ምክንያት ከ240 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተናግሯል።

ኮ/ል ሾሻኒ የእስራኤል ኃይሎች በአሜሪካ ለሚመራው የሰላም ዕቅድ ቁርጠኛ መሆናቸውን ነገር ግን ሐማስ ከአሁን በኋላ በእስራኤል ሰላማዊ ዜጎች ላይ ስጋት እንዳይፈጥር እና አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ በአካባቢው እንደሚቆዩም ተናግረዋል።

"ሐማስ ታጥቆ ጋዛን ለመቆጣጠር እየሞከረ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው" ያሉት ኮሎኔሉ፣ "ይህ መከናወን ያለበት ነገር ቢሆንም እኛ ግን ከዚያ በጣም ርቀናል።"

በጋዛ ከተማ ውስጥ ያሉ ሕንፃዎች ወደ አቧራማ ፍርስራሾች ተቀይረዋል
የምስሉ መግለጫ, በጋዛ ከተማ ውስጥ ያሉ ሕንፃዎች ወደ አቧራ እና ፍርስራሾች ተቀይረዋል

በአሜሪካ የሚመራው ዕቅድ ቀጣዩ እርምጃ ሐማስ ትጥቅ ፈትቶ ሥልጣኑን በፕሬዚደንት ትራምፕ እና በዓለም አቀፍ ታዋቂ ሰዎች ለሚመራው የፍልስጤም ኮሚቴ እንዲያስረክብ ይጠበቃል።

ነገር ግን ኃይሉን እና ትጥቁን ከመፍታት ይልቅ ሐማስ ተቃራኒውን እየሰራ ነበር ሲሊ ኮ/ል ሾሻኒ ይከስሳሉ።

"ሐማስ ራሱን ለማስታጠቅ እየሞከረ ነው፤ የበላይነቱን ለማረጋገጥ፣ በጋዛ ላይ ቁጥጥሩን ለማጠናከር እየሞከረ ነው" ብለዋል።

"በጠራራ ፀሐይ ሰዎችን እየገደለ ነው፤ ይህንን የሚያደርገው ሰላማዊ ዜጎችን ለማሸበር እና በጋዛ ውስጥ ማን አለቃ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ነው። ይህ ስምምነት ሐማስ ትጥቅ እንዲፈታ ጫና ለመፍጠር በቂ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።"

የእስራኤል ወታደሮች ባየናቸው ፍርስራሾች ስር እንዳገኙ የሚናገሩትን የዋሻዎች ካርታ ለጋዜተኞች አሳይተዋል። "ትልቅ የዋሻ መረብ፣ ልክ እንደ ሸረሪት ድር ያለ ነው" በማለት ከፊሉ መውደሙን ከፊሉ ግን አሁንም ባሉበት ይዞታ እንደሚገኙ አንዳንዶቹ ደግሞ አሁንም እየፈለጉ መሆኑን ያብራራሉ።

በዚህ የሰላም ስምምነት የሚቀጥለው ደረጃ ምን እንደሚሆን ግልጽ አይደለም።

ስምምነቱ ጋዛን ውጥረት ውስጥ ጥሏታል። በዋሽንግተን ሁኔታው ምን ያህል ደካማ እንደሆነ ይረዳሉ። የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቀድሞውኑ ሁለት ጊዜ ተጥሷል።

አሜሪካ ከዚህ ከሚዋዥቅ የተኩስ አቁም ወደ ዘላቂ ሰላም ለመሸጋገር ግፊት እያደረገች ነው። ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የተላከ እና ቢቢሲ የተመለከተው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ የጋዛን ፀጥታ ለመቆጣጠር እና ሐማስን ትጥቅ ለማስፈታት ዓለም አቀፍ የሚያረጋጋ ኃይል የሁለት ዓመት ሥልጣንን እንደሚኖረው ይገልጻል።

ነገር ግን የዚህ ቀጣይ የስምምነት ደረጃ ዝርዝሮች በጣም የሳሱ ናቸው። ሐማስን ትጥቅ ከማስፈታት በፊት የትኞቹ አገራት ወታደሮቻቸውን እንደሚልኩ፣ የእስራኤል ወታደሮች መቼ እንደሚወጡ ወይም የጋዛ አዲስ በምሁራን የሚመራው አስተዳደር አባላት እንዴት እንደሚሾሙ ግልፅ አይደለም።

ፕሬዝዳንት ��ራምፕ ጋዛን በውጭ ኢንቨስትመንት የተገነባች የወደፊቷ የመካከለኛው ምሥራቅ ማዕከል አድርገው በመግለፍ ያላቸውን ራዕይ ዘርዝረዋል። ያ ግን ጋዛ ዛሬ ካለችበት በጣም ሩቅ ነው።

በእስራኤል በብዛት የወደሙ እና በትራምፕ እንደ ኢንቨስትመንት የታዩት አካባቢዎች ላይ ያለው ጥያቄ ውጊያውን ማን ሊያስቆመው ይችላል ብቻ ሳይሆን፣ የጋዛ ተወላጆች በወደፊት ማኅበረሰባቸው እና መሬታቸው ላይ ምን ያህል መብት ይኖራቸዋል የሚለው ጭምር ነው።